ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች እንዲመለሱ የኢሶህዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ ወሰነ

by admin · December 2, 2017

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አቻቸው አብዲ መሀመድ ኡመር ጋር በሚያዝያ 2009 ዓ.ም የሰላም ስምምነት በፈረሙበት ወቅት (Photo: Awramba Times)

አውራምባ ታይምስ (ጂግጂጋ) – የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶህዴፖ) ማእከላዊ ኮሚቴና የሀገር ሽማግሌዎች ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ባካሄዱት የጋራ ጉባኤ፣ ቀደም ሲል በጠቅላይ ሚኒስትት ቢሮ በተደረገ ስብሰባ የተወሰደውን አቋም በሙሉ ድምጽ ያጸደቁ ሲሆን በዚህም መሰረት የዚህ ስብሰባ አቋም አንድ አካል የሆነውን ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች በሙሉ ከተፈናቀሉበት ቦታ እንዲመለሱ በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ታውቋል።

ዛሬ በተወሰነው ውሳኔ መሰረት ተመላሾቹ ምንም አይነት እክል እንዳይገጥማቸው የክልሉ መንግስት ፣ የማእከላዊ ኮሚቴው አባላትና የክልሉ ሀገር ሽማግሌዎች ሙሉ ሀላፊነቱን የወሰዱ ሲሆን በዚህ መሰረትም የተፈናቀሉትን ወገኖች ወደ ቄያቸው የመመለስ ተግባር ባፋጣኝ ይጀመራል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ፣ ጉባኤው የሰላም ስራዎችን በማካሄድ በሁለቱ ክልሎች መካከል የተፈጠረውን ቁርሾ የማጥፋትና የሁለቱ ክልል ህዝቦችን የሚያቀራርብ ስራ እንዲሰራ በአጠቃላይ ህገመንግስቱን የማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በሙሉ ድምጽ ወስነዋል።

', enableHover: false, enableTracking: true, buttons: { twitter: {via: ''}}, click: function(api, options){ api.simulateClick(); api.openPopup('twitter'); } }); jQuery('#facebook').sharrre({ share: { facebook: true }, template: '

{total}

', enableHover: false, enableTracking: true, click: function(api, options){ api.simulateClick(); api.openPopup('facebook'); } }); jQuery('#googleplus').sharrre({ share: { googlePlus: true }, template: '

{total}

', enableHover: false, enableTracking: true, urlCurl: 'http://www.awrambatimes.com/wp-content/themes/hueman/js/sharrre.php', click: function(api, options){ api.simulateClick(); api.openPopup('googlePlus'); } }); jQuery('#pinterest').sharrre({ share: { pinterest: true }, template: '

{total}

', enableHover: false, enableTracking: true, buttons: { pinterest: { description: 'ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች እንዲመለሱ የኢሶህዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ ወሰነ',media: 'http://www.awrambatimes.com/wp-content/uploads/Somali-oromia2.jpg' } }, click: function(api, options){ api.simulateClick(); api.openPopup('pinterest'); } }); });

Tagged as:

No tags for this article